Telegram Group Search
የጠፋው በግ

በአንድ ሰሞን አባትና ልጅ ጠባብ በሆነች ሰፈር ይኖሩ ነበር። የአባትየው ስም ገ/ማርያም ሲሆን የልጅየው ስም ደግሞ ዮሴፍ ይባላል እኚህ ቤተሰብ እግዚአብሔርን በማገልገል በፍቅርና በደስታ ይኖሩ ነበር ። አባትየው እግዚአብሔርን የሚያገለግለው በክህነትና በመመምህርነት ሲሆን ልጁ ደግሞ ዘማሪ ነበር። እግዚአብሔርንም በጣም ከመቅረባቸው የተነሳ የሰፈሩ ሰዎች "የእግዚአብሔር ሰዎች" በማለት ነበር የሚጠሯቸው። አባትየው በጡረታ ብር ሲሆን የሚተዳደረው ስራ የለውም ልጁም የአድማስ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ ነው።

ከእለታት በአንዱ ቀን ዮሴፍ ቦርሳውን ታጥቆ ወደ ት/ት ቤት ያመራል በመንገድ ላይም ሳለ አንድ ማንነቱን የማያውቀው ሰው "ሰላም ላንተ ይሁን አለው" እርሱም በመገረም "ላንተም ይሁንልህ" በማለት መለሰለት ከእዚያም ያ ሰው አስከትሎ "ስሜ ኤልያስ ይባላል ስለሆነ ነገር እንድንነጋገር ነበር ወንድም"

👱🏽 ዮሴፍም፡- "መልካም በምን ጉዳይ ነበር?"

👱🏾 ኤልያስ፡- "ሀይማኖታዊ ጉዳይ ነው ወንድም እኔ ኦርቶዶክስ ነበርኩ ግን አሁን ቀጥተኛውን መንገድ እየተከተልኩኝ ስለሆነ ይህችን ወረቀት ተመልከታትና እየተገናኘን እንወያያለን።"

👱🏽 ዮሴፍ፡- "አመሰግናለሁኝ ወንድሜ ግን አያስፈልገኝም እኔ እራሴን አውቃለሁ የድንግልን ልጅ እየመለክሁ የዘላለም ህይወትን አግኝቻለሁ።"

👱🏾ኤልያስ፡- "ይገርማል! ውጪ ውጪውን ነው አይደል ኢየሱስን የምታመልኩ የምትመስሉት ግን ቤተ ክርስቲያን ስሙም ትዝም አይላችሁም።"

👱🏽ዮሴፍ፡- "መልካም ወንድሜ እንዲህ ከሆነ የምታስበው መጀመሪያውኑም ኦርቶዶክስ አልነበርክም ማለት ነው።"

👱🏾ኤልያስ፡- "ማለት??"

👱🏽ዮሴፍ፡- "የተዋህዶ መሰረቷ ማን እንደሆነ ሳታውቅ ነዋ የጠፋኸው!"

👱🏾ኤልያስ፡- "ማን ነው መሰረቷ ደግሞ? "

👱🏽ዮሴፍ፡- "መሰረቷ እርሱ ክርስቶስ ነው።"

👱🏾ኤልያስ፡- "ድንቅ ነው እሺ መሰረቷ ክርስቶስ ነው እንበል ማርያምስ አማላጅ ናት??"

👱🏽ዮሴፍ፡- "በሚገባ"

👱🏾ኤልያስ፡- "ጥሩ! ይሄው እንካ ከእዚህ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ 'ማርያም አማላጅ ናት' የሚል ጥቅስ አምጣልኝ።"

👱🏽ዮሴፍ፡- "አሁን ጥቅሱ የቱ ጋር እንዳለ አላውቅም ነገ አንብቤ አመጣልሀለሁ።"

👱🏾ኤልያስ፡- "እሺ ጥሩ ነገ በእዚሁ ሰአት እዚህ ካፌ እንገናኝ።"

👱🏽ዮሴፍ፡- "አሁን እንደምታየኝ ወደ ት/ት እየሄድኩ ነው እናም በእዚህ ሰአት ስለማይመቸኝ ከክላስ ስወጣ 8፡00 ሰአት አካባቢ እንገናኝ።"

👱🏾ኤልያስ፡- "በቃ ነገ 8፡00 ሰአት እንገናኛለን እንወያያለን ሰላም ዋል! "

👱🏽ዮሴፍ፡- "እሺ ወንድም ሰላም ዋል!"

ዮሴፍም ወደ ትምህርት ቤት መንገዱን አመራ። ታክሲ ውስጥም ተቀምጦ ሳለ ስለዚሁ ነገር እያሰበ ነበር በውስጡም "አዎን በእርግጥ ድንግል ማርያም ታማልዳለች ግን ይህንን ጥቅስ ከየት ነው የማመጣለት? አባን ልጠይቀው እንዴ አይ! ስለዚህ ነገር ከነገኩት ለምን ቆመህ አወራህ ብሎ ይቆጣኛል። ግን እራሴው ማርያም አማላጅ ናት የሚል ቃል ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ እፈልጋለሁ" አለ።

ትምህርቱንም አጠናቆ ወደ ቤቱ አመራ ቤት እንደገባም የመጀመሪያ ስራው መፅሀፍ ቅዱሱን ከፀሎት ቤት ማምጣት ነበር። ከእዚያም መክሰሱን ካጠናቀቀ በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ፀሎትን አቅርቦ መፅሀፍ ቅዱሱን ገልጦ ማንበብ ጀመረ በመጀመሪያ ያነበበው መፅሀፍ የሉቃስን ወንጌል ነበር። ምክንያቱም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ይናገራል ብሎ ያሰበበትና የተማረውም እሱን ነበር።

ስለ ዘካሪያስ አነበበ ሄደ ስለ ድንግል ማርያም የሚናገረው የምእራፍ ቁጥል ላይ ሲደርስ "ማርያም አማላጅ ናት" የሚል ቃል በቃል የተፃፈን ጥቅስ መፈለግ ጀመረ ያነበበው ይህን ነበር 👇👇👇

ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝²⁶ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
²⁷ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
²⁸ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
²⁹ እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና፦ ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
³⁰ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
³¹ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
³² እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
³³ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
³⁴ ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
³⁵ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
³⁶ እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
³⁷ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
³⁸ ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
³⁹ ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥❞

"እስካሁን ድረስ 'ማርያም አማላጅ ናት' የሚል ቃል የለም ግን ወደ መጨረሻው አገኘዋለሁ" ብሎ ምርመራውን ቀጠለ

ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝³⁹ ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
⁴⁰ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
⁴¹ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
⁴² በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
⁴³ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
⁴⁴ እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
⁴⁵ ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
⁴⁶ ማርያምም እንዲህ አለች፦
⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
⁴⁹ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
⁵⁰ ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
⁵¹ በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
⁵² ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
⁵³ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
⁵⁴-⁵⁵ ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
⁵⁶ ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።❞

ይህንንም በጨረሰ ጊዜ የዮሴፍ ልብ ታወከ ደነገጠም በልቡም እንዲህ ብሎ አሰበ "ማርያም አማላጅ ናት የሚል የለምምም! ይህ ምን ማለት ነው??? አቤን ልጠይቀው? አይ ይናደድብኛል ስለዚህ ምን ባደርግ ይሻላል" ብሎ በልቡ ስለዚህ ነገር እያሰበ ወደ ውጪ ወጣ!

ይቀጥላል
ተግባራዊ ክርስትና

ፀሎት ብቻ አይደለም
ስግደትና ፆም ብቻ አይደለም

ተግባራዊ ክርስትና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነትና ህይወትም ጭምር ነው። ብዙዎቻችን በውስጣችን ቂም አዝለን ከሰው ተጣልተንና ለሰው ፍቅር ሳይኖረን በፀሎትና ፆም ብቻ ክርስትናችንን የተገበርን ይመስለናል።

እግዚአብሔር አምላክ ይህንን አይወድም ቅዱስ ዮሀንስም በመልእክቱ "የሚታየውን ወንድምህን ሳትወድ የማይታየውን እግዚአብሔር እወዳለሁ ትላለህን? ይለናል።

ጌታችንም እንዲሆናችሁ "መፅሀፍትን ትመረምራላችሁ እነሱም ስለኔ ይናገራሉ ግን ህይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ወደኔ ልትመጡ አትወዱም።" ይለናል ይህ ቃል ምንድን ነው?

ጠቢብ ነን ምሁር ነን ብዙ አንብበናል ብዙም ነገር አውቀናል ክርስትና ገብቶናል ምዕመኖቻችንን ከመናፍቃንና ከአህዛብ እንጠብቃለን የሚሉ ክርስቲያኖች ህይወታቸው እንዴት ነው?

ከወንድማቸው ከክርስቲያኑ ጋር ያላቸው ግንኙነትስ? እውቀታቸው ትምክህት ሆኖባቸው ፀጋቸው መታበያ ሆኖባቸው እግዚአብሔር ፀጋና እውቀቱን የነጠቃቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም።

እግዚአብሔር የልብን መታደስ የሚፈልግ አምላክ ነው ልብና ኩላሊትም ሚመረምረው ጌታ ከኛ ትህትናን ራስን ዝቅ ማድረግንና እንደ ቃሉ መመላለስን ይፈልግል።

ይሄን ስናደርግ ፀሎታችንም ፆማችንም ዝማሬያችንም ይሰማል መላእክትም ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ያግዙናል ይራዱናል።🙏🙏
የአዳዲስ የተዋህዶ መዝሙሮችን በየእለቱ የሚለቅላችሁ የተዋህዶ ቻናል

የተዋህዶ መዝሙሮች ቤት
ይቀላቀሉን

@eotcholysong
የጠፋው በግ
ክፍል ሁለት ( ፪)

ዮሴፍም ወደ ውጪ ወጥቶ በማሰላሰል ላይ እያለ አባቱ ነገረ ሁኔታውን በማስተዋል ተከትሎት ወጣና

አባት፡- " ልጄ ምነው ችግር አለ?"

ልጅ፡- " አይ አባ ነገ ማርኬቲንግ ፈተና ስላለኝ ጨንቆኝ ነው።"

አባት፡- " እርግጠኛ ነህ ልጄ የዛሬው ሁኔታህ ከሌላው ቀን የተለየ ነው ብዬ ነው ንገረኝ ልጄ ምን ሆነህ ነው?"

ልጅ፡- "ኧረ አባዬ መስሎህ ነው እንጂ ሌላ ነገር የለም ፈተና ሲደርስ ሁሌም ይጨንቀኛል እሱን ታውቃለህ አባባ"

ብሎም አስከትሎ "መሽቷል አባባ እንግባ" በማለት ወሬውን ለማስረሳት ሞከረ አባትየውም አንድ ነገር እንዳለና ሊነግረው እንዳልፈለገ በመረዳት "መልካም ልጄ ይሁን" አለው። ከገቡም በኋላ ዮሴፍ መፅሀፍ ቅዱሱን ይዞ በድጋሚ ወደ መኝታ ቤቱ ገባና የመንፈስ ቅዱስ ፀሎቱን አድርጎ መፅሀፉን ገልጦ ማንበብ ጀመረ። እንዲህ ሲልም በልቡ አሰበ "እውነት ማርያም አማላጅ ናት የሚል ቃል መፅሀፍ ቅዱስ ከሌለ ያልጅ ያለኝ ነገር ትክክል ነው ማለት ነው" አለና በድጋሚ በጩኸት "ይቅር ይበለኝ ምን ሆኜ ነው" አለ።

የቤቱ ሰራተኛም ጩኸቱን ሰምታ "አቡሽ ጠራኸኝ" በማለት ወደ መኝታ ቤቱ መጣች። እርሱም "አይ አልጠራሁሽም እህቴ ለምለም አመሰግናለሁ!" አላት አሷም "እሺ መልካም አቡሽ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ጥራኝ" በማለት ስራዋን ቀጠለች። ዮሴፍም መፅሀፉን ገልጦ ስለሌላ ነገር ሲያወራና ሲቃዥ መፅሀፉን ማቃለሉን ተረድቶ በስርአት መፅሀፉን ማንበብ ቀጠለ ከእዚያም «ማርያም አማላጅ ናት የሚል ቃል ፍለጋ መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን ላይ ገለጠ አነበበ አነበበ የዮሴፍ ፍለጋ ቃል በቃል ነውና ማግኘት አልቻለም ይህም ሌላ ጭንቀት ሆነበት "እሺ የዮሀንስ ራእይ ላይ ልፈልግ ብሎ እርሱን ገለጠ።

በድጋሚም ቃል በቃል ስለሆነ ፍለጋው ቃሉን ሊያገኘው አልቻለም የዮሴፍ ጭንቀት በረታ የሚገባበት አጣ እጅጉን ፈራ " 'ማርያም ታማልዳለች' የሚል ቃል ከሌል አታማልድም ማለት ነው? ሎቱ ስብሐት ምን ሆኜ ነው ይህን ያህል ከምጨነቅ ለምንድን ለምለምን ጠርቼ አልጠይቃትም?" ብሎ አሰበ ከእዚያም የቤታቸውን ሰራተኛ ለምለምን ጠራት።"

ዮሴፍ፡- "ለምለም ለምለም!"

ለምለም፡- "ጠራኸኝ አቡሽ?"

ዮሴፍ፡- "አዎን ጠርቼሽ ነው ይቅርታ ከስራ አቋረጥኩሽ?"

ለምለም፡- "አላቋረጥከኝም አቡሽ ምን ፈልገህ ነው ምን ላምጣልህ?"

ዮሴፍ፡- "አይ የኔ እህት ጥያቄ ልጠይቅሽ ፈልጌ ነበር.... "

ለምለም፡- "ምን አይነት ጥያቄ አቡሽ?"

ዮሴፍ፡- "ሀይማኖታዊ ነው!"

ለምለም፡- "እሺ ጠይቀኝ አቡሽ" ብላ ተቀመጠች

ዮሴፍ፡- "አንዱ ጓደኛዬ ስለ ማርያም ምልጃ ማወቅ ፈልጎ 'ማርያም አማላጅ ናት' የሚል የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ጠይቆኝ ነውና የቱ ጋር እንደሆነ ታውቂያለሽ??

ለምለም፡- "መጀመሪያ ይህ ምን አይነት ጥያቄ ነው አቡሽ? አንድ ነገር ማስተዋል አለብህ መፅሀፍ ቅዱስ እኛ እንደምንፈልገው ሳይሆን እግዚአብሔር እኛ እንድናውቀው በፈለገው መንገድ ነው የተፃፈው ስለዚህ አንድም ሰው አንድን ነገር ለማረጋገጥ ቃል በቃል የተፃፈ ሊያገኝ አይችልም ምክንያቱም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣም እግዚአብሔር የገለጠልንን እኛው በመንፈስ ቅዱስ ልንረዳው ይገባናል እንጂ!"

ዮሴፍ፡- "ስለዚህ ለምለም እህቴ ልትይኝ የፈለግሽው ማርያም አማላጅ ናት የሚለውን ሳይሆን ስለ ምልጃዋ በሌላ ቃላት የተፃፈውን ቦታ ነው መፈለግ ያለብን?"

ለምለም፡- "በሚገባ"

ዮሴፍ፡- "ይገርማል እሺ ለምለም እህቴ ስለ ድንግል ማርያም ምልጃ የሚናገሩ ጥቅሶች ትነግሪኛለሽ?"

ለምለም፡- "እስኪ አቡሽ ከመንገሬ በፊት አማላጅ ማለት ምን ማለት ነው?"

ዮሴፍ፡- "አማላጅ ማለት አስታራቂ በሁለት አካል መሀል ሆኖ የሚማልድ ወይንም ስለ ሀጢአት የሚለምን ማለት ነው።"

ለምለም፡- "እሺ መልካም አቡሽ አሁን መፅሀፍ ቅዱስ በእጅህ ላይ አለ 2ቆሮ 5፥20 ላይ ምን ይላል አንብብልኝ።"

ዮሴፍ፡- "❝እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።❞

ለምለም፡- "እዚህ ጋር እንደምንመለከተው ብርሀነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔር በእኛ ይማለዳል እያለ ነው ይህም እኛ ወደ እግዚአብሔር እንለምናለን ከእግዚአብሄር ጋር ታረቁ ብለን ሁላችን ወደ እግዚአብሔር እንፀልያለን ማለት ነው ??? "

ዮሴፍ፡- "አዎን ሁላችንም ለእግዚአብሔር እንለምናለን"

ለምለም፡- "መልካም አሁን ያዕ 5፥16 ላይ ያለውን አንብብና ጥያቄውን ራስህው ትመልሰዋለህ እስኪ ምን ይላል?"

ዮሴፍ፡- "❝እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።❞ ይህ ማለት እኔ ስለ አንቺ አንቺም ስለ እኔ መፀለይ ትችያለሽ ግን ከሁለታችን ይልቅ ፀሎቷ የሚሰማ ድንግል ማርያም ስለኛ ብትፀልይልን ፀሎቷ እጅጉን ይሰማል ማለት ነው። ስለዚህ ይህ ጥስቅ ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ይናገራል ማለት ነው።

ለምለም፡- "አዎን አቡሽ ግን ይህን ሁሉ ጋሼን መጠየቅ ትችል ነበር ለምን አልጠየቅከውም?"

ዮሴፍ፡- "ፈርቼው ነው እህት ለምለም"

ለምለም፡- "ብትጠይቃቸው እንደው ደስ እያላቸው ነበር የሚመልሱልህ።"

ዮሴፍ፡- "ጥያቄው ከኔ ቢመጣ ኖሮ አዎን!"

ለምለም፡- "ጓደኛህ ስላላወቀ ነው የጠየቀህ አንተም ስላልተረዳህ ብትጠይቃቸው ጋሼ በደስታ ይመልሱልህ ነበር"

ዮሴፍ፡- "አይደለም! ለምለም እህት ያልገባሽ ነገር አለ ልጁ ጓደኛዬ አይደለም ዛሬ ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ መንገድ ላይ አቁሞ ነው አናግሮኝ በመጨረሻ ይህንን ጥያቄ የጠየቀኝ"

ለምለም፡- "አቡሽ! ስለምን እንዲህ አደረግህ ? ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነትንም ሆነ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ለመመስከር አውቀህ መገኘት አለብህ ግን ስለዛ ነገር ካላወቅክ ጥያቄውን በራስህ ለመመለስ እንዳትሞክር ስንቱ በእዚህ ምክንያት ጠፍተዋል ግን መንፈስ ቅዱስ አብዝቶ የተመሉ መምህራን ካህናትና የቤተ ክርስቲያን ዲያቆናትን ጠይቅ ኒቆዲሞስ እንኳ መምህር ሆኖ በለሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየሄደ ይማር ነበር አንተም እንዲሁ አድርግ።!

ዮሴፍ፡- "አትጥፋ ያለኝ አምላክ ዛሬ በእዚች ሰአት አንቺን ልኮ ገሰፀኝ መከረኝ ከጥፋትም አዳነኝ ከመምጣትሽ ከጥቂት ደቂቃ በፊት ይህ ስሜት ውስጤ አልነበረም አይምሮዬ ስቶ ነበር ግን ሀይሉ አንቺን እጠራ ዘንድ አዘዘኝ! እግዚአብሔር ይመስገን" አለና ወደ አማኑኤል ስእለ አድኖ ዞር ብሎ እጅ ነሳ

ለምለም፡- "እኔ ምንም አላደረግሁም አቡሽ ይህ እንዲሁ ተድበስብሶ አልፏል ግን ከአባ ምንም ልትደብቅ ዘንድ አይገባም!"

ዮሴፍ፡- "እሺ አመሰግናለሁ"

ለምለም፡- "መልካም እራት የማቀርብበት ሰአት እየደረሰ ስለሆነ ወደ ሳሎን ዝለቅና ለአባም የደበቅሐቸውን ነገር ትነግራቸዋለህ።"

ዮሴፍ፡- "እሺ አመሰግናለሁ ለምለም እህት መጥቼ ስለሁሉም ነገር እነግረዋለሁኝ።"

ለምለም፡- "መልካም"

ይቀጥላል..........
የጠፋው በግ

ክፍል ሶስት (፫)

ዮሴፍም መፅሀፍ ቅዱሱን ወደ ፀሎት ከመለሰ በኋላ ወደ ሳሎን ዘለቀ አባቱም "ና ልጄ ተቀመጥ" አለው። ዮሴፍም የደበቀውን ነገር ሊነግረው ወሰነና ሶፋው ላይ ከጎኑ ተቀመጠ እንዲህም ሲል ንግግሩን ጀመረ...


ዮሴፍ፡- "አባ"

አባት፡- "ወዬ ልጄ ምንድነው?"

ዮሴፍ፡- "ስለ አንድ ነገር ልነግርህ ነበር ግን እንዳትናደድ?"

አባት፡- "ስለምን እናደዳለሁ ልጄ ንገረኝ!"

ዮሴፍም የተፈጠረውን ነገር ሁሉ በተጨማሪም ከለምለም ጋር ያወራውን ነገር ሁሉ ነገረው ከእዚያም

ዮሴፍ፡- "መጀመሪያ ላንተ ባለመንገሬ ይቅርታ አድርግልኝ አጥፍቻለሁ!"

አባት፡- "የኔ ልጅ ትልቁ ጥፋትህ ለኔ አለመናገርህ ሳይሆን ጥያቄውን ራስህ መርምረህ ለመመለስ መሞከርህ ነው። ይህንን ትምህርት ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አስተምሬዋለሁኝ ጥያቄውን እንደተጠየቅህ መጥተህ ብትጠይቀኝ ደስ እያለኝ አስተምርህ ነበር ግን አንተ ከእኔ ቁጣ ለመሸሸግ ብለህ ሁሉንም በራስህ ለመመለስ ሞከርክ ከእዚህ በፊት ስለዚህ ጉዳይ እውቀናው ቢኖርህ መልካም ነበር ነገር አንድን ነገር አጥርተህ ሳትረዳ ለማስረዳት የለብህም ይህ ነገር እንዳይደገም።"

ዮሴፍ፡- "እሺ አባ ሁለተኛ እንዲህ አይነት ጥፋት አላጠፋም ይቅር በለኝ!"

አባት፡- "ጥፋቱ የሚጎዳው ከእኔ ይልቅ አንተን ነው ልጄ ምክንያቱም በእዚህ ምክንያት የአንተም ነፍስ ልትጠፋ ነበር በል አሁን መሽቷልና እራታችንን በልተን እንተኛ።" አለው

ዮሴፍም ያደረገውን ጥፋት በማስተዋል ዳግመኛ እንዲህ ያለ ጥፋት አላጠፋም ብሎ ለራሱ ቃል ገባ አሁን ነፍሱ አርፋለች በሰላምና በደስታ እራቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ መኝታ ቤቱ ሄዶ ተኛ።

ሁለተኛ ቀን

ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቃ ሁሌም ጠዋት እንደሚያደርገው ወደ ፀሎት ቤትም ገብቶ  መልከአ መድሐኔዓለም ና ውዳሴ ማርያም አነበበ ከእዚያም ፀሎቱን እንደጨረሰ "እሰይ ነጋ" የሚለውን የሊቀ መዝሙራን የቴዎድሮስን መዝሙር ከፍቶ ምስጋናውን ቀጠለ። ምስጋናውንም እንደጨረሰ ቁርሱን ተመገበና ወደ ትምህርት ቤት ሄደ። ዮሴፍ በመሄድ ላይ ሳለም በልቡ እንዲህ ብሎ አሰበ "እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ ከትምህርት መልስ ኤፍሬምን አገኘዋለሁ ስለገባኝም በደንብ አድርጌ አስረዳዋለሁ።" አለ

ትምህርት ቤትም ተማረ የመውጫው ሰአት ሲደርስ ከትምህርት ቤት ወጣ ከኤፍሬምም ጋር የሚገናኝበት ሰአት ሲደርስ ትላንትም የተገናኙበት ቦታ ሄደ። ኤፍሬምም ቁጭ ብሎ እየጠበቀው ነበር እንደተገናኙም

ኤፍሬም፡- "ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ"

ዮሴፍ፡- "ላንተም ይሁን ሰላም ነው?"

ኤፍሬም፡- "እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ"

ዮሴፍ፡- "መልካም"

ኤፍሬም፡- "እሺ ተቀመጥ!"

ዮሴፍ፡- "አመሰግናለሁ"

ኤፍሬም፡- "እሺ ወንድሜ ሻይ እየጠጣን እንወያይ" አለና ሻይ አዘዘ ውይይቱንም እንዲህ ሲል ጀመረ።
"እሺ እንግዲህ ያው ሁለታችንም በተቀጣጠርነው ሰአት ተገኝተናልና ውይይታችንን እንጀምር ትላንት በውይይት መሀል የጠየቅኩህ ጥያቄ ነበር ይህም 'ማርያም አማላጅ ናት' የሚል ጥቅስ እንድታሳየኝ ነበር። አንተም ዛሬ የቀጠርከኝ በእዚሁ ጉዳን በደንብ እንድንነጋገር ነውና ጥቅሱን ካገኘህ ጀምር!"

ዮሴፍ፡- "እሺ ጥሩ ወንድም ከመፅሀፍ ቅዱስ አፃፃፍ እንጀምርና እኛ የመፅሀፍ ቅዱስ ተከታዮች ነን እና መፅሀፍ ቅዱስ እንዳስረዳን እንጂ እኛ እንደፈለግነው አልተፃፈም ለምሳሌ አምላካችን መድሐኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ወንጌሉ ይናገራል ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ላይ 'እኔ አምላካችሁ ነኝ አምልኩኝ!' ብሏል?? አላለም ግን ከተናገረው ቃላትና ድርጊቶት ከአብ ጋር የተተካከለ መሆኑን ፈጣሪ መሆኑን እንድንረዳ ያደርገናል። እስካሁን ድረስ ማለት የፈለግኩት ነገር ገብቶሀል አይደል???"

ኤፍሬም፡- "አዎን መፅሐፉ እኛ እንደፈለግነው ሳይሆን እሱ እንዳስረዳን መጓዝ እንዳለብን ነገሮችን ቃላቶችን አገጣጥመን ማግኘት እንዳለብን።"

ዮሴፍ፡- "በጣም ደስ ይላል ጥሩ ተረድተኸኛል ማለት ነው አሁን ይህንኑ ሀሳብ ወደ ድንግል አማላጅነት እንውሰደው ክርስቶስ ኢየሱስ አምላክ ነኝ አምልኩኝ ብሎ አልተናገረም ግን ነገረ ስራዎቹ አለም ሳይፈጠር ዘመን  ሳይቆጠር እንደነበረና ከተናገረው ንግግር እራሱ እግዚአብሄር መሆኑን ለመረዳት ችለናል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅ ናት ተብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈ የለም ግን ቅድም እንዳልኩህ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃላቶችን ስናገጣጥምና በመንፈስ ቅዱስ ሆነን ስንረዳ የማርያም አማላጅነት ይገባናል። የምታነሳው ሀሳብ ወይንም ካልኩት ነገር ትክክል አይደለም ብለህ የምታስበው ነገር አለ?"

ኤፍሬም፡- "የለም እየተረዳውህ ነው ቀጥል!"

ዮሴፍ፡- "እሺ ስለ አማላጅነቷ ከማንሳታችን በፊት አማላጅ ማለት ምን ማለት ነው?"

ኤፍሬም፡- "አማላጅ ማለት በሁለት ሰዎች መሀል ቆሞ የሚያስታርቅ ወይንም ስለ አንዱ አካል የሚለምን ማለት ነው።"

ዮሴፍ፡- "በጣም ጥሩ አሁን በእጅህ ላይ ያለውን መፅሀፍ ቅዱስ ግለጥና 2ቆሮ 5፥20 ላይ ያለውን ጥቅስ አብብልኝ"

ኤፍሬም፡- ❝እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።❞

ዮሴፍ፡- "ቃሉን ስንተነትነው እዚህ ጋር ቅዱስ ጳውሎስ ምንድነው እያለ ያለው?"

ኤፍሬም፡- "እኛ ወደ እግዚአብሄር ማላጆች ስንሆን ከእግዚአብሄር ጋር ታረቁ እንላለን እኛ ወደ እግዚአብሄር አማላጆች ነን እያለ ነው።"

ዮሴፍ፡- "እሺ መልካም አሁን ፃድቃኖች ሁሉ ወደ እግዚአብሄር እንደሚያማልዱ ቃሉ ይናጋራል ማለት ነው አይደል?"

ኤፍሬም፡- "አዎ"

ዮሴፍ፡- "ስለዚህ ፃድቃን ታረቁ ብለው ከለመኑ ከፃድቃኖች የምትፀድቀው ድንግል ማርያም ደግም እንዴትስ አስበልጣ አታማልድም?"

ኤፍሬም፡- "ድንግል ማርያም አሁን ስለኛ ታማልዳለች ማለት ነው?"

ዮሴፍ፡- "ቃሉ ይህን ይላል ያመነ ይጠቀማል ያላመነ ግን ትልቅ ነገርን አጉድሏል ድንግል ማርያም ዘላለማዊ አማላጅ ናት! "

ኤፍሬም፡- "ያልከውን ነገር ተረድቻለሁ ግን ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ያስፈልገኛል ቀኝና ግራን መመልከት አለብኝ ወንድም ግን ጥሩ ማብራሪያ ሰጥተኸኛል።"

ዮሴፍ፡- "እሺ መልካም ይሁን ዋናው ቃሉንና እኔ ያልኩህን ነገር መረዳትህ ነው ስለዚህ ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል ውስጥህ ይስራ ይህን ካሰብክ በኋላ መልስህን ታሳውቀኛለህ።"

ኤፈሬም፡- "እሺ መልካም ስልክ እንለዋወጥና እንዲሁ እየተገናኘን እንወያያለን አስፈላጊ ሰው ትመስላለህ!" አለና ስልኩን ሰጠው ዮሴፍም ሰጠውና ውይይታቸውን እንዲሁ ጨርሰው ተለያዩ።

ይቀጥላል.....
የድንግል ማርያም እረፍት
ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ አርጋኖን ድርሰቱ ከሚያሰጥመው ባሕር ሞገድ የተነሣ የማትነቀነቅ፥ መልኅቆቿም በሦስቱ ሥላሴ ገመድ የተሸረቡ ናቸው ይህቺ ደግሞ ከነፋሳት ኃይል የተነሣ የማትናወጥ በጭንጫ ላይ ያለች የዕንቈ ባሕርይ ምሰሶ ናት፤ እርሷን የተጠጋ መውደቅ መሰናከል የለበትም” የሚላት እመቤታችን ሞት አይቀርምና እርሷም እንደሰው የምትሞትበት ጊዜ ደረሰ፡፡ እግዚአብሔር አያዳላምና፡፡ /ሮሜ.፪፥፲፩/2፥11/ ቅድስት ድንግል ማርያም የኃያሉ እግዚአብሔር እናቱ፥ መቅደሱ፥ ታቦቱ፥ መንበሩ ሆና እያለ ሞትን መቅመሷ በራሱ የሚያስገርም ምሥጢር ነው፡፡ ከቤተ ክርስትያን ወገን ሞትን እንዳያዩ የተወሰዱ ቅዱሳን ሄኖክ፥ ኤልያስ፥ ሌሎችም እንዳሉ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት አለ፡፡ ይህ ከኅሊናት ሁሉ በላይ የሆነው ምሥጢር ርቀቱ በመጽሐፈ ዚቅ እንዲህ ተብሏል፡፡ “ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ ኢያድለወ  ሞት ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ፡፡ ኃይለኛ በኃይሉ ለምን ይታጀራል? ባለ ጸጋም በሀብቱ ብዛት፡፡ ክርስቶስ ለአካሉ አላዳላም፤ ሞትስ ለሟች ይገባዋል የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ሞት ግን አስደናቂ ነው”
እመቤታችን ያረፈችው በጥር ሃያ አንድ ቀን ነው፤ በአባት በእናቷ ቤት ሦስት ዓመት ኖረች፤ ዐሠራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፤ ከልጇ ጋር ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወራት፤ ከጌታ ስቅለት በኋላ ዐሥራ አምስት ዓመታት ኖረች፤ ጌታን የጸነሰችበትን ወራት ስንጨምር በዚህ ዓለም በሥጋ የቆየችበት ጊዜ ስድሳ አራት ዓመት ይሆናል፡፡
የቤተ ክርስቲያን ትውፊት የድንግል ማርያም ሞት በሚከተሉት ምክንያቶች እንደሆነ ያስረዳል፤ የመጀመሪያው “ለመለኮት ማደርያ ለመሆን የበቃችው ኃይል አርያማዊት ብትሆን ነው እንዷ ምድራዊት ሴትማ እንደምን ሰማይና ምድር የማይችለውን ልትሸከመው ይቻላታል?” የሚሉ ወገኖች ነበሩና በርግጥም እግዚአብሔር ወልድ የተዋሐደው የሰው ልጆችን ሥጋ እንጂ የመላእክትን አለመሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስረዳ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥በሕይወታቸው ሁሉ ስለሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፡፡ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” አለ፡፡ /ዕብ.፪፥፲፬-፲፭/2፥14-15/ በዚህም ድንግል ማርያም የአዳም ዘር መሆኗ ታወቀ፡፡ ሁለተኛው ቅዱስ ያሬድ እንዳለው ጌታችን በፍርዱ አድልዎ የሌለበት መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በለበሰው ሥጋ ሞትን ይቀምስ ዘንድ የግድ ነውና፡፡ ይህን በማስመልከት ጥር 21 አንድ ቀንን የእመቤታችንን እረፍት እናከብራለን።

ወስባሐት ለእግዚአብሔር..
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺 እንኳን አደረሳችሁ !! 🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
Audio
" የእግዚአብሔር ፈቃድ "

በመምህር ሳሙኤል አስረስ

መልካም ቆይታ🥀🥀
የጠፋው በግ

ክፍል አራት (፬)

እንደተለያዩም ዮሴፍ በንግግራቸውና በመለሰው መልስ ረክቶ ስለነበር በደስታ ወደ ቤቱ አመራ ግን በተቃራኒው ኤፍሬም ግራ ተጋብቶ ነበር ምክንያቱም ከብዙ አመታት በፊት የማያውቃቸው ሰዎች በመንገድ ላይ ሳለ ጠርተውት በእዚህ ጉዳይ ጥያቄ እንዳቀረቡለት እንዲሁም መልስ ሲያጣ ሀይማኖቱ ልክ አይደለም ብሎ እንደወጠና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ልክ አይደለችም ብሎ የያዘው መረጃ ይህው ጉዳይ ስለነበር ነው ።

ኤፍሬም ስለዚሁ ጉዳት እያሰላሰለ ወደ ቸርች ሄደ ስብከት አዳመጠ ሲመሽም ወደ ቤቱ ገባ ቤትም እንደደረሰ ውስጡ ደጋግሞ መፅሀፍ አንብብ መፅሀፍ አንብብ ይለው ጀመር ቁጭ ብሎ መፅሀፉን ገልጦም ማንበብ ጀመረ። ስለ ብዙ ነገር አነበበ ግን ውስጡ ያለውን ጥያቄ ሊመልስለት አልቻለም ዮሴፍ ስላስረዳው ነገር ደጋግሞ ያስብ ነበርና በልቡ እንዲህ አለ "እኔ ከኦርቶዶክስ እምነት የወጣሁት ማርያም አታማልድም ብዬ ነው ግን አሁን አማላጅነቷን መፅሀፍ ቅዱሱ ካስረዳኝ ያኔ ተሳስቼ ነበር ማለት ነው?? ኦርቶዶክስ ስልክ ነበረች ማለት ነው እንዲህ ከሆነ!!!" አለና ተኛ ። ደግሞ በነጋታው ከቤቱ ወጣና ወደ ጓደኛው ቤት አመራ።

ኤፍሬምም ጓደኛው ቤት እንደደረሰ "ሰላም ላንተ ይሁን ብሎ" ገባ ጓደኛውም ኤፍሬምን ካየው ቆይቶ ስለነበር "የት ጠፍተህ ነው ኤፍሬም እንዴት ነህ ግን" አለው

ኤፍሬምም፡- "አለሁ ናቲ ትንሽ ስራ በዝቶብኝ ነው ሰሞኑን ያልመጣሁት"

ናቲ፡- "ችግር የለውም ዋናው በሰላም መሆኑ ነው!"

ኤፍሬም፡- "መልካም ናቲ ስለሆነ ነገር ላናግርህ ነበር አሁን ማትወጣ ከሆነ"

ናቲ፡- "አዎ ዛሬ ምንም አይነት ቀጠሮ የለብኝ ኤፍሬም መወያየት እንችላለን"

ኤፍሬም፡- "አንተ ስላልነበርክበት ላታውቀው ትችላለህ ግን እኔ ከኦርቶዶክስ እምነት የወጣሁት 'ማርያም አማላጅ አይደለችም' ብዬ እንደሆነ ታውቃለህ......"

ናቲ፡- "አዎን በመንገድ ላይ የሆኑ ሰዎች አግንተውህ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንደመሩህ ነግረኸኛል! እና?"

ኤፍሬም፡- "ሳስበው አሁን በጣም ትልቅ ስህተት ተሳስቻለሁኝ ማለትም በአንድ ነገር ላይ እርግጠኛ ሳልሆንና እውቀቱ ሳይኖረኝ ወደ ውሳኔ መሄድ የለብኝም ነበር በእርግጥ አሁን ኦርቶዶክስ ሆኛለው እያልኩኝ ሳይሆን አርቶዶክስ ስለ ማርያም ምልጃ ልክ መሆኗን አውቄያለሁ ይህም ስቼ የሄድኩበት ምክንያት ልክ እንዳልሆነ ይነግረኛል።

ናቲ፡- "አልገባኝም ኤፍሬም 'ማርያም አማላጅ ናት' እያልከኝ ነው? ይህን እንዴት ልትቀበል ቻልክ እሷ ያለችበት ቦታ አለ ወይንስ የመሰከረላት ሰው አለ?"

ኤፍሬምም ቁጭ አድርጎ መፅህፍ ቅዱሱን አስገለጠውና ዮሴፍ ያስረዳውን በሙሉ ለናትናኤል አስረዳው ገሰፀው። ናትናኤልም እንደ ኤፍሬም እጅጉን አልደነገጠም ምክንያቱም እሱ ከተወለደ ጀምሮ ስለ ማርያም ተነግሮት አያውም ስለ ምልጃዋም ተከራክሮ አያቅም ስለዚም ማርያም ታማልዳለች የሚለው መረጃ ለሱ ብዙም ድንቅ አልነበረም።

ናቲ፡- "ይገርማል ግን ብዙም አያስደንቅም ግን በደንብ ማረጋገጥ ይገባናል ስለ ማርያም ምልጃ ይህን ጥቅስ ብቻ መረጃ ማድረግ አንችልም።"

ኤፍሬም፡- "እሺ ለምሳሌ? ምን ማፍረሻ ቃል ይኖረናል ናቲ ሁላችንም ማማለድ እንችላለን እኮ ነው የሚለው ቃሉ!"

ናቲ፡- "አዎ እሱማ ቃሉ እርስ በእርስ እንድንፀልይ ያዛል"

ኤፍሬም፡- "ታዲኛ ሁላችንም ማማለድ ከቻልን ድንግል ማርያም አምላክን በሆድዋ ለመሸከም የከበረች ሴት እንዴት አታማልድም ?? "

ናቲ፡- "እኔንጃ ኤፍሬም እኔ ስለዚህ ነገር ብዙም እውቀቱ የለኝም ሻል ያለ ሰው ጠይቅ።" አለውና ውይይቱን ለማቋረጥ "ሻይ እንድታፈላልን እህቴን ነግሬያት መጣው ብሎት ወደ ውጪ ፈጠን ፈጠን እያለ ወጣ።

ኤፍሬምም "ይህ እንዲሁ የሚያበቃ ነገር አይደለም የሀይማኖት መምህራችንንማ መጠየቅ አለብኝ አለና ጥሎት ወደ ቸርች ሄደ ታክሲ ውስጥ እያለም ሹፌሩ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የቴዎድሮስ "ከፍቅሯ ርቃችሁ የምትኖሩ" የሚለውን መዝሙር ከፍ ባለ ድምፅ ከፍቶት ነበር። ኤፍሬምም ይህንን መዝሙር ሲያዳምጥ አይምሮውን ይበልጥ ጭንቅ አለው እንኳን የድንግል ማርያም ፍቅርን ሊቀበል ቀርቶ ስለ ምልጃዋ በሰማው ነገር እየተርበተበተ ነው።

ከታክሲም ወረደ በፍጥነት ወደ ቸርች ሲገባ "ሐዋአያ የተባለ ገ/ዮሀንስ" ሰባኪ ትምህርት በመስጠት ላይ ነበር። ኤፍሬምም ቁጭ ብሎ ተከታተለ በትእግስትም እስኪጨርስ ድረስ ጠበቀና ስብከቱን ከጨረሰ በኋላ

ኤፍሬም፡- "መምህር ስለ አንድ ጉዳይ ላናግሮት ነበር?"

መምህር፡- "እሺ ልጅ ኤፍሬም እንኳን ወደ እግዚአብሄር ቤት መጣህ ምን ልትጠይቀኝ ትፈልጋለህ?"

ኤፍሬም፡- "መልካም መምህር ስለ ማርያም ምልጃ ነበር።"

መምህር፡- "እሺ ቁጭ በል"

ኤፍሬም፡- "መምህር አንተ ማርያም አማላጅ አይደለችም ያልከው በምን ተነስተህ ነው?"

መምህር፡- "የተፃፈ የለም!"

ኤፍሬም፡- "ስለ ምልጃዋ ስላልተፃፈ ብቻ ነው ማርያም አማላጅ አይደለችም ያልከው ወይስ.....?"

መምህር፡- "በእርግጥ ስላልተፃፈ ብቻ ሳይሆን አማላጅ ናት ብንል እንኳ ሞታለች የሞተ ሰው ደግሞ አያማልድም።"

ኤፍሬም፡- "ማለት በክርስትና ሞት በስጋ ነው በነፍስ???"

መምህር፡- "በእርግጥ በስጋ ነው ግን የሞተ ሰው ምንም አያውቅም።"

ኤፍሬምም ተገረመ ምክንያቱም የማርያምን አማላጅነት ሊያፈርስ የሚችል መረጃ ይህ ነው ብሎ ይነግረኛል ብሎ አላሰበም አንድ ክርስቲያን ሁለት ውልደት እንዳለው መልካም ከሰራ አንድ ሞትን ብቻ ይሞታል ይህም በስጋ ብቻ ነው ነፍስ ግን ዘላለማዊ እንደሆነችና ሁሉንም ነገር በደንብ አድርጋ እንደምታውቅ ያውቅ ነበር።

ኤፍሬም፡- "እሺ መምህር ባልከው ነገር ላይ አንድ ጥያቄ አለኝ የሞተ ሰው ምንም ነገር አያቅም ካልክ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው የመጀመሪያው መልእክት ላይ ዛሬ ና ነገ ብሎ ከሞት በፊት በከፊሉ እንደሚያውቅና ከሞት በኋላ ደግሞ ሁሉን በደንብ እንደሚያውቅ ይናገራል እና ይህ ነገር አንተ ካልከው ነገር ጋር ይሄዳል??"

መምህር፡- "አትሳሳት የእኔ ልጅ ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ እንደሚሻለው ሁሉ ከሞተ ፃድቃን ያልሞተ ሀጢአን ይሻላል።"

ኤፍሬም፡- " እሺ መልካም መምህር ግን ይህ ቅዱስ ጳውሎስ ከተናገረው ቃል ጋር ይስማማል? እኔ እስከማውቀው ከሆነ መምህር እኔ ከሞትኩ በኋላ አሁን ከማውቀው ይበልጥ እንደማውቅ ነው ይህንንም የምልህ ይህንን ቃል መሰረት አድርጌ ነው።

❝ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።❞
—1ኛ ቆሮንቶስ 13: 12 መምህር ስህተት ካለብኝ አርመኝ

መምህር፡- "ይህ ታዲያ ስለ አማላጅነት ይናገራል ልጄ?"

ኤፍሬም፡- "አይናገርም ግን መምህር...." እንዳለም ከአፉ ነጥቆ

መምህር፡- "ስለዚህ አታማልድም ማለት ነው። ጥሩ ውይይት ነበረን ልጄ ሌሎችም ጥያቄ ካሉህ ልትጠይቀኝ ትችላለህ ሰላም ዋል!" አለውና ከቸርቹ ውጣና ሄደ።

ይቀጥላል.......
የጠፋው በግ

ክፍል አምስት (፭)

ኤፍሬምም መልካም አለና ወደ ጓደኛው ናቲ ቤት ተመለሰ ወደ ቤት ደርሶ እንደገባም

ናቲ፡- "ኤፍሬም በሰላም ነው ሳትነግረኝ ብን ብለህ የጠፋኸው?"

ኤፍሬም፡- "መምህር ገ/ዮሀንስን ላናግረው ሄጄ ነበር።"

ናቲ፡- "አይ መልካም እና መልስ ሰጠህ?"

ኤፍሬም፡- "አልሰጠኝም ጭራሽ የማይታመን ተረት ነገረኝ ይቅርታ መምህር ስለሆነ ስለሱ እንዲህ ማለት የለብኝም ነገር ግን ምክንያት ሊሆን የማይችለውን ምክንያት ጠቅሶ ማርያም አታማልድም አለኝ።"

ናቲ፡- "ምን ጠቅሶ ነው"

ኤፍሬም፡- "እሱማ ያለው 'ሰው ከሞተ በኋላ ምንም ነገር አያቅም' ነው።"

ናቲ፡- "እና ዳዲ ኮ እውነቱን ነው።"

ኤፍሬም፡- "ምን እያልክ ነው ናቲ እኛ ብንሞት ምንም ዋጋ የለንም ማለት ነው??"

ናቲ፡- "እንደሱ እንኳን አይመስለኝም።"

ኤፍሬም፡- "አሁንስ ድክም አለኝ" ብሎ ሶፋው ላይ ተዘርግቶ ተኛ ድካም ላይ ስለነበር በእዛው እንቅልፍ ወሰደው።

ኤፍሬም ህልሙ እንዲህ ነበር
«ህልሙም እንደጀመረ አይኑን ጨፍኖ ነበር ልክ እንደገለጠው ያለበት ስፍራ በአረንጓዴ ሳር የተሞላ ነበር ብዙ ዛፎችም ስለነበሩ ስፍራው ጫካ ነገር ይመስል ነበር ይህንንም ተመልክቶ ቀና እንዳለ አንዲት ቀይ ሴት በምስራቅ በኩል ቆማ ተመለመተ ቀሚሷ እንደ ወተት የነጣ ተበረ ሰውነቷም እንደ ጨረቃ ያበራ ነበር። ሊቀርባት ሲፈልግ እግሩ በጥቁር ገመድ ታስሮ ነበርና አልቻለም። ያያታል እርሷም እርሱን እየተመለከተች ትናገራለች ግን ድምጿ አይሰማውም ከእሩቅ ሆና አፏ ሲንቀሳቀስ ይታየዋል እርሱን እየተመለከተች ስትናገርም ደግሞ እየተናገረች ያለችው ለእርሱ እንደሆነ ያስተውላል። ኤፍሬምም በእዚሁን ሰአት ገመዱን ለመፍታት አጥብቆ ፈለገ ግን አልቻለም እና "አንጋጦ ማነሽ ምን እያልሽኝ ነው?" እያለ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ። እናም በለቅሶው መሀል ገመዱ ከእግሩ ላይ ሲፈታ ተመለከተ ማን እየፈታው እንዳለ አይታየውም ግን ገመዱ እየተፈታ ነበር። ገመዱ ተፈቶ እንደጨረሰም በድጋጤም ወደተመለከታት ቀይ ሴት እየሮጠ ሄደ እርሷም ስትለው የነበረውን በቀረባት ጊዜ አስተውሎ ሰማው እንዲህም ስትለው ነበር “ልጄ አትሽሸኝ ና እናትህ ነኝ” የሚል ነበር ድምጿንም ደግሞም ሰማው በድጋሚም እንዲህ ትል ነበር “ልጄ አትሽሸኝ ና እናትህ ነኝ” ይል ነበር በደንብ እየቀረባት መጣ ቀርቧትም አጠገቧ ሲደርስ» ከእንቅልፉ ነቃ በጣም ደነገጠ እንዴት ያለ ህልም ነው ብሎ ተጨነቀ ። ናቲም ኤፍሬም በድንጋጤ ከእንቅልፉ ሲነቃ ተመልክቶ

ናቲ፡- "ምነው ኤፍሬም ደህና ነህ?" አለው

ኤፍሬም፡- "ናቲ ህልም አይደለም ያየሁት።" አለው በድንጋጤ እያለከለከ

ናቲ፡- "ምንድነው ምን አይተህ ነው?"

ኤፍሬም፡- "አይ ምንም አይደል!" አለና ተነስቶ በፍጥነት ወደ ውጪ ወጣ። በረንዳ ላይ ቆሞም ለመረጋጋት እየሞከረ እንዳለ የውስጥ መንፈሱ «ለዮሴፍ ደውል ለዮሴፍ ደውል» አለው ስልኩንም አውጥቶ ደወለለት። የተነጋገሩትም ይህን ነበር

ኤፍሬም፡- " ሄሎ! "

ዮሴፍ፡- "ሄሎ ኤፍሬም"

ኤፍሬም፡- "ሰላም ነው ዮሴፍ እንዴት ነህ?"

ዮሴፍ፡- "እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ አንተስ ደህና ነህ?"

ኤፍሬም፡- "እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ አመሰግናለሁ።"

ዮሴፍ፡- "መልካም ወንድም በሰላም ነው?"

ኤፍሬም፡- "አዎን በሰላም ስለ ባለፈው ጉዳይ እንድንወያይ ነበር እና ዛሬ ብንገናኝ ይመችሀል?"

ዮሴፍ፡- "መልካም ግን ዛሬ አይመቸኝም ወንድም ምናልባት ነገ ከተመቸህ ክላስ ስለሌለኝ መገናኘት እንችላለን"

ኤፍሬም፡- "እሺ ጥሩ ነገ ከሰአት በኋላ ስራ ስለምለቀል በባለፈው ቦታ እንገናኛለን"

ዮሴፍ፡- "እሺ ወንድሜ ደህና ሁን"

ኤፍሬም፡- "እሺ አመሰግናለሁ ደህና ሁን" ብሎ ስልኩን እንደዘጋው ናቲ ከየት መጣ ሳይባል ፊት ለፊቱ ተደቅኖ

ናቲ፡- "አንተ ልጅ ግን ዛሬ ምን ሆነሀል??" ብሎ ጠየቀው

ኤፍሬምም፡- "ምንም አልሆንኩም ናቲ ዝም ብለህ አታስብ አሁን እየመሸ ስለሆነ ወደ ቤት ልሂድ ቀኑ የሚያደክም ስለሆነ ነገ ለስራ ልዘጋጅ በደንብ ማረፍ አለብኝ።"

ናቲ፡- "እስካሁን ስለ ማርያም አማላጅነት እያሰብክ ባልሆነ ቀኑ የደከመህ ስለዚህ ነገር ስትጨነቅ ነው? ማርያም እንደሆነች አታማልድም ይህን ያህል ያስጨነቀህ ግን ለምን እንደሆነ አልገባኝም!"

ኤፍሬም፡- "አዎን አንተ ቀምሰኸው ስለማታውቀው አታውቀው ይሆናል ሰላም እደር ቻው።" ብሎ ወደ ውጭው በር አመራ

ናቲ፡- "ምን ማለት ነው ኤፍሬም ማለት የፈለከው አልገባኝም?"

ኤፍሬም፡- "ግልፅ የሆነ ቃል ነው ቻው እደውልልሀለው።" አለና ወጥቶ በሩን ዘጋው። ናቲም ሁኔታው እጅጉ አስገርሞት በውስጡ እንዲህ አለ "ይሄ ልጅ ዛሬ በጤና አይደለም እንዲህ የተርበተበተው የሆነ ያልነገረኝ ነገርማ አለ" ።

ኤፍሬምም ወደ ቤቱ እንደገባ እህቱን እራት ጠይቆ ወዲያው በልቶ ተኛ ውስጡ ድካም ስለነበር ለሊቱን ሙሉ ያለ መንቃት እስከ ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ ተኛ። ከእንቅልፉ ሲነቃ አይምሮውን በትንሹ ቅልል ብሎታል ተነሳና ለስራ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ቦታው አመራ ። ሲሰራ ሲሰራም ውሎ የመለቀቂያ ሰአቱ በደረሰ ጊዜ ልቡ ድንጋጤውን ጀመረ ትላንት የነበረው ስሜት በከፊሉ እየተሰማው መጣ ምክንያቱም ከትንሽ ሰአታት በኋላ ዮሴፍን ሊያገኘው ነውና

ይቀጥላል...........
የጠፋው በግ

ክፍል ስድስት (፮)

ከስራም እንደወጣ ለዮሴፍ ደወለለት

ኤፍሬም፡- " ሄሎ ዮሴፍ"

ዮሴፍ፡- "ሄሎ ኤፍሬም ሰላም ነው ልደውልልህ ነበር!

ኤፍሬም፡- "እግዚአብሔር ይመስገን አለሁኝ እዛው ካፌ እንገናኝ"

ዮሴፍ፡- "እሺ መልካም"

ሁለቱም በቦታው ደረሱ ሰላም ተባባሉና ጠቀመጡ። ዮሴፍም ኤፍሬም ለምን ደግሞ እንደጠራው ከማወቅ በጉጉት ጆሮውን ከፍቶ ከኤፍሬም የሚወጣውን ቃል ይጠባበቅ ነበር። ኤፍሬምም ከየትና ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶታል። ዮሴፍም እንዲህ ብሎ ውይይቱን ጀመረ

ዮሴፍ፡- "እሺ ወንድሜ ኤፍሬም ድጋሚ የቀጠርከኝ በምን ጉዳይ ልታነጋግረኝ ነው?"

ኤፍሬም፡- "ታስታውሳለህ በመጀመሪያ ቀን መንገድ ላይ አግኝቼህ 'ኦርቶዶክስ ነበርኩኝ' ያልኩህን ነገር?"

ዮሴፍ፡- "አዎን አስታውሳለሁ"

ኤፍሬም፡- "እና የወጣሁበት ምክንያት ምንድን እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ?"

ዮሴፍ፡- "አዎ ምንድነው?"

ኤፍሬም፡- "ማርያም አማላጅ ናት የሚል ጥቅስ አምጣ ተብዬ ስላጣሁ ነው!"

ዮሴፍ፡- "ግን ይህ ጥያቄ እኮ....." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ኤፍሬም ቅምት አድርጎ

ኤፍሬም፡- "አዎ ትክክል እንዳልሆነ አውቃለው እሱ ጋር ነው የተሳሳትኩት ግን ስለ አንተ ግራ የገባኝ ነገር ይህን ጥያቄ ሳቀርብልህ ወዲያውኑ ጥያቄው ትክክል አይደለም አላልከኝም ነበር 'ጥቅሱ ጠፍቶብኛል ነገ አመጣለሁ' ነበር ያልከኝ ከእዛም በማግስቱ ነው ሁሉንም ያብራራህልኝ ግን ይህን ሁሉ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?" አለው

ዮሴፍም አንገቱን ደፋና "ይህ ለእኔ ቀላል ነገር አልነበረም በጣም ትልቅ ሙግት ውስጥ ነበርኩ ጥያቄውን እንደጠየቅከኝ ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ቃል በቃል 'ማርያም አማላጅ ናት' የሚለውን ጥቅስ እየፈለግኩ ነበር ከእዛም ሳጣው 'አታማልድም ማለት ነው' ብዬ የምንፍቅና ንግግር መናገር ጀመርኩኝ ከእዚያም....." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ

ኤፍሬም፡- "ከእዛስ ምን አደረግክ???"

ዮሴፍም ይህ የጥድፊያ ጥያቄ አስገረመውና የሆነውን ነገር ሁሉ አንዳችም ሳያስቀር ነገረው ለትንሽ ሰከንዶች ያህል ክህደት ላይ እንደነበርና የቤታቸው ሰራተኛ እንደገሰፀችሁም እንዲሁም አባቱ ስለመከረውም ጭምር ሁሉንም ነገር ነገረው በመጨረሻም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለው።

ዮሴፍ፡- "ብዙዎቻችን የኦርቶዶክስት ተዋህዶ ምእመናን የምንሳትበት መንገድ ይህ ነው ጥያቄን ሳናስተውል በራሳችን መመለስን እንፈልጋለን በእዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኑን እናቃልላለን ከእናት ቤታችን ወጥተን ክህደትን ተላብሰን ተዋህዶን ከምድር የምናጠፋ ወታደር እንሆናለን ይህ ሁሉ የሚሆነው መፅሀፍ ቅዱስ ስለማናነብና አባቶቻችንን ስለማንጠይቅ ነው እኔ ለስሙ አባቴ የቤተ ክርስቲያን መምህር ነው ግን እኔ ምድ አደረግሁ? እርሱ ይቆጣኛል ብዬ በመፍራት ሳላስበው ነፍሴን ላጠፋት ነበር።"

ኤፍሬምም በነገረው ነገር እጅጉን ተደነቀ ውስጡም "አላወቅከውም እንጂ እዚህ ከአጠገብህ የተቀመጠው ሰው ጳውሎስ ነው የህይወትን ፍሬ እየመሰከረልህ ነው አዎን እውነት ነው እውነት ነው ጥቁሩ ገመድ ተፈትቷል እራስህን አግኝተሀል አንተ ኦርቶዶክስ ነህ እናትህ ድንግል ናት እርሷም አማላጅህ ናት ይህን ተቀበል አትሞኝ ኤፍሬም " አለው ራሱን ማግኘቱን አረጋገጠ በጣም ተደሰተ ከወንበሩም ተነሳና ዮሴፍን ጥብቅ አድርጎ አቀፈው ከአይኑም እምባ ጠብ ጠብ ይል ነበር ።

ዮሴፍም የኤፍሬም አኳኋን አስገርሞት

ዮሴፍ፡- "ወንድሜ ምነው በሰላም ነው?"

ኤፍሬም፡- ...................

ዮሴፍ፡- "ወንድሜ ደህና ነህ ለምን አትመልስልኝም??"

ኤፍሬም፡- "አመሰግናለሁ።"

ዮሴፍ፡- "ለምኑ ነው የምታመሰግነኝ?" እንዳለውም

ኤፍሬም ለቆት ተቀመጠና እንዲህ አለው "እኔንና አንተን እግዚአብሄር ፈተና ፈትኖናል ሁለታችንም ደንግጠናል ግራ ተጋብተናል የምንፍቅና ሀሳብ ተመላልሶብናል እኔ በሀጢአቴ ጠፋው ግን አንተ ፀንተህ ቆምክ ፈተናውን አለፍክ ግን አልፈክ የጠፋውን ዝም አላልከውም ቀጠሮን መሰረዝ ትችል ነበር ግን አንተ እኔ ጠፍቼ ላጠፋህ የነበርኩትን ዳግመኛ ልትገስፀኝ መጣህ።"

ዮሴፍም በንግግሩ በጣም አሳዘነውና "ወንድሜ" ብሎ ኤፍሬምን አቀፈው ኤፍሬምም በጣም ደስ አለው እንደ አዲስ የተፈጠረ ያህል ተሰማው።

ዮሴፍ፡- "እሺ ወንድሜ አሁን ከእኛ ዘንድ ነህ እግዚአብሔር ይመስገን ቸርነቱ ብዙ ነውና የጠፋው በግ በእኔ እጅ ይድን ዘንድ እኔን ወደ አንተ ላከ።"

ኤፍሬም፡- "እውነት ነው ወንድሜ እግዚአብሔር ለዘለአለም ይመስገን ይክበር ፍጥረታት ሁሉ ለእርሱ ይገዙለት ከአሁን በኋላ ጓደኛሞች ነን አብረን ሆነን የበግ ለምድ የለበሰውን ሁሉ እንገፋለን ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን ተዋህዶ ትክክለኛ እምነት እንደሆነች ለአለም እናውጃለን።"

ዮሴፍ፡- "እሺ ወንድሜ በጣም ደስ ይለኛል ተባረክ"

ኤፍሬም፡- "አሜን! እና አሁን ወዴት ነህ?

ዮሴፍ፡- "ወደ ቤት አንተስ?"

ኤፍሬም፡- "ቤት ከሄድክ በኋላስ?"

ዮሴፍ፡- "ቤት ከገባው በኋላ ደግሜ ቤተ ክርስቲያን እሄዳለሁ አንተስ? ?"

ኤፍሬም፡- "እኔ የትም አልሄድም ወደ ቤትህ አብሬህ ልምጣና ከአባትህና ከአገልጋያችሁ ለምለም ጋር ታስተዋውቀኛለህ...... ችግር የለውም አይደል?"

ዮሴፍ፡- "ኧረ ምንም ችግር የለውም አሁንኮ ጓደኛሞች ነን ቤተሰቤን ባስተዋውቅህ ደስ ይለኛል"

ኤፍሬም፡- "እሺ እንሂዳ"

ዮሴፍ፡- "መልካም"

ከእዚያም ወደ ቤቱ ወሰደው ከአባቱና ከአገልጋያቸው ለምለም ጋር አስተዋወቀው ለአባቱና ለአገልጋዩም ስለ ኤፍሬምም ነገራቸው ማን እንደሆነና በምን መልክ እንዳወቀው እንዲሁም የምንፍቅና ህይወት ላይ እንደነበረ አሁን ግን እንደዳነም ጭምር ሁሉንም ነገራቸው። እነርሱም እግዚአብሔርን አመሰገኑ አቤት ያንተ ስራ እያሉ ለብዙ ሰአታት ያህል ምሥጋናን አቀረቡ። ዮሴፍም ይህንን ሲመለከት ይበልጥ በውስጡ ሀሴት አደረገ የጠፋው በግ ተገኝቷልና እግዚአብሔርን ከእነርሱ ጋር ሆኖ አመሰገነ ።

ተፈፀመ
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️

በእዚህ የልቦለድ ታሪክ ላይ አስተያየት ካሎት በእዚህ user name 👉 @MeronJC ሊያሳውቁን ይችላሉ።
ፈረስ በብረት ልጓም ይገታል። የሕዝብም ልጓሙ ንጉሥ ነው። መቃብር መልካም ጐታ ነው ብስሉንና ጥሬውን ይከታልና። ወዳጅ ቢወዱት ይወዳል መሬትም ቢበሉት ይበላል።....(መሬት የበቀለውን እንበላለንና)

          
  ቁም ነገሩ
👇👇👇
"፤ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል እኔ ግን እላችዋለሁ ጠላቶቻችሁን መርቁ ለሚያሳዱዱችሁ ጠልዮ

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?

ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? "

(የማቴዎስ ወንጌል 5÷ 43-47)
Channel photo updated
ሁላችሁም የተዋህዶ ልጆች ይህንን ምስል ፕሮፋይላችሁ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሀዘንና ስብራት እንግለፅ።

በፆመ ነነዌም ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በፆም በፀሎት ስለ ቤተክርስቲያናችን ወደ እግዚአብሔር እንጩህ። 🙏🙏😔
Audio
🔵 ይህ አይገባትም

🔸ሊቀ መዘመራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ🔸

@eotcholysong
2024/04/30 23:28:18
Back to Top
HTML Embed Code: